ተጠራጠር ትወድቃለህ አሸናፊነትን አስብ ይሳካልሀል

ምን ልትሰራ እያሰብክ ነው ? እያሰብሽ ያለሽው ነገር እንደሚሳካልሽ ታምኚያለሽ ?። ብዙዎቻችን እኛ እንደሚሆንልን ያላመነውን ነገር ሰዎች እንዲቀበሉት እንጀምራለን። እንደማይሆንልን እንደምንሸነፍ የምናስበው እኛው ነን። ከራሳችን በላይ ለራሳችን ማንም ጠላት የለም የሚለው አባባል የሚገልፀው ይመስለኛል። ታድያ በዚህ አስተሳሰብ ጭንቅላታችንን ወጥረን እንዴት ሊሳካልን ነው?።


የምናምነው ነገር (Belief) ውጤታችን ላይ ትልቅ ተፅእኖ አለው። ይሄን የተዛባ እምነታችንን መቀየር ውጤታችንን ይቀይራል። ትዳር እንደምትመሰርት ፣ ቤት እንደምትሰራ ፣ መኪና እንደሚኖርህ ፣ ሐብታም እንደምትሆን ፤ ዶክተር ፣ መሐንዲስ ፣ መምህር ፣ አርቲስት ፣ ባለስልጣን ፣ የሐይማኖት ሰው ፣ ወታደር ፣ ነጋዴ ፣ ሞዴል ወዘተ…ያሰብከውን እንደምትሆን በቅድምያ አንተ ማመን አለብህ።


ለመስራት ያሰበውን ነገር እንደሚሳካለት እያሰበ የሚሰራ ሰው እና በጥርጣሬ በፍርሃት የተሞላ ሰው እኩል ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም። ዶ\ር ዴቪድ ሽዋርዝ (David Schwartz) ትልቅ የማሰብ ጥበብ “The magic of thinking big” ባለው መፅሐፉ ላይ እንዳሰፈረው

በጥርጣሬ ማሰብህ ለውድቀት

አሸናፊነት ማሰብህ ለስኬት ያበቃሀል።

“Think doubt and fail
Think Victory and Succeed”


ዶ\ር ዴቪድ በዚህ መፅሐፉ ስለ ማመን አብዝቶ ይወተውተናል። እንደሚሳካልህ አስብ ዋላ ላይ እንደማይሆንልኝኮ አውቀው ነበር የሚል አገላለፅህ እንዳይከተል አለማመንን አስወግድ እንደሚሆንልህ አስቀድመህ አመን ይለናል። ይሄ የይሆናል እምነት እንዴት እንደምትሰራው መንገዱን እንድትመርምር ያደርግሃል ።

ቀላል ምሳሌ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ/ናዝሬት መሄድ የፈለገ ሰው አዳማ እንደሚደርስ ያምናል ከዛ በምን አይነት መንገድ መሄድ እንደሚችል ያጣራል በቀለበት መንገድ ይሁን በዋናው አዳማ ከች ይላል። መሄዱን ማመኑ ምን ያክል ጊዜ ይፈጃል ? የትኛው ምን ያክል ገንዘብ ያስከፍላል ? ።


እምነት የማይዳሰስ ነው። ውጤቱም ዘግይቶ የሚታይ በመሆኑ ለታይታ ስለማይመች ብዙ ሰው ትኩረት በመስጠት ላይገነባው ይችላል። በተለይ እንደኛ አለመቻልህ ደጋግሞ በሚነገርበት እና መቻልህ እንደ ጉራም በሚቆጠርበት ማህበረሰብ እንደምትችል ማመን ቀላል አይደለም::

እምነት ትልቅ ጉልበት (power) አለው። እምነት የየትኛውም ሀይማኖት መሰረት መሆኑን እናስብ ሀይማኖትን ያለ አምነት ማሰብ አይቻልም። ተራራን የማፍለስ ተግባር እምነት ይጠይቃል። ህሙማን የሚፈወሱት ዐይነ ስውራን የሚያዩት በእምነት በኩል በሚያልፍ የፈጣሪ ይሁንታ ነው። እምነት ሐይል አለው::


“ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም።” ከልብ ለማልቀስ ደግሞ ከልብ መፈለግ ይጠይቃል። ልክ እንደዛው ከልብ ፈልጎ ተግባራዊ ለማድረግ መስራት የፈለግነው ነገር ውጤታማ እንደሚሆን ማመን አለብን። ቤት ለመስራት ፣ ትዳር ለመመስረት ፣ ትምህርት ጨርሶ ለመመረቅ ፣ ድልት ምችት ያለ ኑሮ ለመኖር ፣ በሀይማኖት ጠንካር ለመሆን የጀመርሽውን ጉዞ ማመን አለብሽ ጉዞው እንደሚሳካልህ በአጅህ እደምታስገባው ማመን አለብህ።


አንተ ይሄን ከማመንህ በፊት ማንም ሊያምንልህ እና ሊቀበልህ አይችልም። የስኬት ጉዞው መነሻው መድረሻውም ባንቺ ተፀንሶ ካንቺው የሚወለድ የእምነት እዳ ነው። እምነታችን የሌሎችን ሰዎች ጥንካሬ ርህራሄ ፍቅር ይስባል። ከጊዜያቸው ከንብረታቸው አልፈው ሰዎች ራሳቸውን እስከመስጠት የሚደርሱልን በኛ የእምነት ጥንካሬ መስታወትነት ነው።

በተቃራኒው በስኬት መንገዳችን አለማመን ጥርጣሬ ጉልበታችንን ያደክማል። እንደማይሳካልህ የምታስብ ሲሆን ያለመሳካት መንገዶች ይመጡብሃል በደንብ ተጠራርተው መንገድ ይዘጉብሃል።

“Disbelief is negative power. When the mind disbelieves or doubts, the mind attracts “reasons” to support the disbelief. Doubt, disbelief, the subconscious will to fail, the not really wanting to succeed, is responsible for most failures.” The Magic of Thinking Big by David J Schwartz

በአለማችን ላይ የምናያቸው ታላላቅ የፈጠራ ውጤቶች ባላመኑና በተጠራጠሩ ሰዎች ሳይሆን ይሆናል ብለው ባመኑ ሰዎች የተሳኩ ናቸው የማብራት ፣ የስልክ ፣ የአውሮፕላን ፣ የበይነ መረብ ወዘተ በይሆናል እምነት በታገሉ ሰዎች የተፈለሰፉ ናቸው።የካንሰር መድሀኒት ሊገኝ ይችላል ብለው የሚያምኑ ሰዎች ዛሬም ከፍተኛ የሳይንስ ምርምር ላይ ተጠምደዋል። ህዋ ላይ ሰዎች ይኖራሉ የሚል እምነት ያላቸው እንደ አሎን ማስክ (Elon Musk) አይነት ሰዎች ዛሬ የስፔስ በረራ ድርጅት (SpaceX) አቋቁመው ሰውን ወደ ህዋ ለማመላለስ ሙከራ ላይ ናቸው። የሰው ልጅ አእምሮ አደርገዋለው ብሎ ያልከወነው ነገር የለም የማመንና ያለማመን ጉዳይ ነው።

እናም ያሰብከው ትልቅ ነገር እንደሚሆንልህ እመን በአእምሮ ውስጥ መጨረሻውን ተመልከት (“Begin the end in mind”)። ያንን ስታምን መንገዶች ይከፈትሉሃል ምክንያቱም ያን ለማሳካት ጥረትህን መቀጠል መንገዶችን መፈለግ ላይ ታተኩራለህና።


ማመንን ለማዳበር 3ቱ የዶ/ር ዲቪድ መፍትሄዎች ስኬትን አስብ ውድቀትን አታስብ ፣ አንተ ለራስህ ግምት ከሰጠኽው የተሻልክ እንደሆንክ አስብ እና ስኬትህ በእምነት ስለሚወሰን ትልቅ ነገር ይሆንልኛል ብለህ እመን።

ትችላለህ

ትችያልሽ

እችላለሁ

እንችላለን


You CAN

I CAN

We CAN

#ashruka #ashrukaacademy