ነፃ የትምህርት እድል ለማግኘት ማወቅ ያለባችሁ ወሳኝ ነጥቦች - Guide

የነፃ ትምህርት እድል ማግኘት ትፈልጋላችሁ ግን ብዙ ባለማወቃችሁ ግራ ተጋብችሁ ይሆናል። ይሄው ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነጥቦች (scholarship guide) አቅርቤላችዋለው።


Eden Fistum Studied at Strathmore University

በየአመቱ በተለይ ባደጉት ሐገሮችና በተለያዩ አለም አቀፋዊም ሆነ ግለሰባዊ ድርጅቶች ነጻ የትምህርት እድሎች ይሰጣሉ ፡፡ እኛን ፍለጋ የሚኳትኑትን እነዚያን እድሎች ለመጠቀም ታድያ አስቀድመን ቀጥሎ የተጠቀሱትን 7 ነገሮች ልብ ማለቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

1. የትምህርት እድል (Admission) እና የገንዘብ እድል (Scholarship) የተለያዩ ነገሮች ናቸው

በነጻ የትምህርት እድል አለም ሁለቱ የትምህርት ምዝገባ (Admission) እና የገንዘብ እድል (Scholarship) )የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡


የትምህርት ምዝገባ የምንለው በአብዛኛው ወደ ትምህርት ተቋሙ ተመዝግቦ ለመማር በቅድምያ የተቋሙን የትምህርት የማመልከቻ ጊዜ ገደብ (admission deadline date) ጠብቆ ማመልከትን ይመለከታል። የገንዘብ እድሉ የሚገኘው ስልጠና ላይ ወይም ትምህርት ላይ ለማዋል ነው ይህም ስኮላርሺፕ የምንለው ነው። እድሉ የትምህርት ቤት ምዝገባ ወጪን ፣ የትራንስፖርት ፣ የምግብ እና የቤት ኪራይ ወጪዎችን ሊያካትት ይችላል።ባብዛኛው ሁለቱንም በተለያየ ማመልከቻዎች በማስገባት ልናገኝ እንችላለን። ትምህርቱን ለመመዝገብ ለትምህርቱ ብቁ የሚያደርገንን ማመልከቻ (Admission Application) ማድረግ ይኖርብናል። የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት የነጻ ገንዘብ ተጠቃሚ ማመልከቻ ( scholarship application) መላክ ይስፈልጋል ፡፡


ሁለቱን ማመልከቻዎች መላክ ወይም አለመላክ እንደ ዉድድሩ ጥሪ ይወሰናል ፤ ይህ ማለት እንዳንድ ጥሪዎች (ማስታወቅያዎች) ሁለቱንም ማመልከቻዎች በተናጥል እንድናስገባ ይጠይቃሉ ወይም ለትምህርት ምዝገባ (admission) ብቁ ከሆንን በቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ ስለምናገኝ የትምህርት ምዝገባ ማምልከቻ ብቻ እንድናስገባ ይጠይቃሉ ።


ይህ በመሆኑም የነጻ የትምህርት እድል መረጃዎች ጋር ስንገናኝ ማስታወቂያው የትምህርት ምዝገባ ነው (admission application call) ወይስ የገንዘብ ድጋፍ ነው (scholarship application call) የሚለውን መለየት ቀዳሚ ተግባር መሆን ይገባዋል ።


ለምሳሌ፦ Education for Sustainable Development (ESED) Scholarship Program የተባለ ድርጅት የሚቀበለው የገንዘብ ድጋፍ ማመልከቻ ብቻ ነው ስለሆነም ለትምህርት ምዝገባ ወደሌላ ተቋም ማመልክት ይኖርብናል ።


በተቃራኒው Erasmus Mundus Programme ለተሰኘ ፕሮግራም የትምህርት ምዝገባ ማመልከቻ መላክ ብቻ በቂ ነው ፤ ለትምህርት ምዝገባ (admission) ከታለፈ ቀጥታ (by default) የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል ። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን ልዩነት ማወቁ ጊዜንም ጉልበትንም ይቆጥባል ።

2. የትምህርት ማስረጃዎች እና የቋንቋ እውቀት ማረጋገጫዎች ዝግጅት (Preparing Documents)

የነጻ የትምህርት እድል ለማግኘት የሚያስፈልጉ ትምህርት ነክ እና ተዛማች መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦

  • Degree Certificate

  • Official Transcript (or sometimes grade reports)

  • Two or more Recommendation letters of your instructor or a company (የመምህር ወይም የስራ ሐላፊ ምስክርነት)

  • Motivation letter (የእድሉ ጠቀሜታ ለግለሰቡ ምን ያክል አስፈላጊ እንደሆነ እና የግለሰቡ ችሎታ የሚያስረዳ የአንድ ወይም ሁለት ገጽ ማብራሪያ)

  • Certificate of Participation in different NGO's or clubs in your community or education center

  • Curriculum Vitea (CV)

  • Passport ወይም Identity Card (ID)


የነጻ የትምህርት እድል ለማግኘት የሚያስፈልጉ የቋንቋ መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦

  • English proficiency letter ( ከዩንቨርሲቲ ሬጅስትራር የሚገኝ)

  • IELTS exam certificate

  • TOEFL exam certificate እና ሌሎችም

ከላይ ከተጠቀሱት ማስረጃዎች በተጨማሪ የ Scholastic Aptitude Test (SAT) ፈተና ውጤት (በተለይ ለዩኤስ አሜሪካ)የመሳሰሉ መረጃዎች ሊጠየቁ ይችላሉ ።

ማሳሰብያ: እንግሊዘኛ ቋንቋ ፈተናን በተመለከተ አለም አቀፍ ፈተና አስፈላጊ ነው ተብሎ እስካልተገለጸ ድረስ የነጻ የትምህርት እድል ተጠቃሚ ለመሆን IETLS ወይም TOEFL መፈተን ግዴታ አይደለም ነገር ግን እንደኔ እምነት እነዚህን ፈተናዎች መፈተን የተሻለ የነጻ የትምህርት እድል እንድናገኝ ያደርጋል።

3. ማመልከቻው በፖስታ ወይም በመረጃ መረብ መሆኑን መለየት (Means of Application)

በአሁን ጊዚ አብዛኛው ውድድር ማስታወቂያ በመረጃ መረብ (Internet) የሚለቀቅና ሁሉም ነገር በቀጥታ ማመልከቻ (online application) የሚጠናቀቅ ነው ።


ነገር ግን በአንዳንድ ውድድሮች በከፊል የትምህርት እና የእንግሊዘኛ ፈተና ማስረጃዎች ቀጥታ በተማርንባቸው ተቋማት ጭምር በፖስታ እንዲላኩላቸው የሚፈልጉ አወዳዳሪዎች ስላሉ አስቀድሞ መለየቱ ከመንከራተት ይታደጋል ።4.ነጻ የትምህርት እድል ለማግኘት ገንዘብ መክፈል ያስፈልጋል ?

በጥቅሉ ሲታይ እድሉን ለማግኘት ክፍያ አያስፈልግም :: ነገር ግን አንዳንድ ዩንቨርሲቲዎች የማመልከቻ ክፍያ (application fee) ይጠይቃሉ::


ይሁን እንጂ በተለይ ከኢትዮጽያ የውጪ ሐገር ክፍያ በግለሰብ ደረጃ የሚፈቅድ ስርዓት ባለመኖሩ ይህን ክፍያ ከኢትዮጵያ መፈጸም አይቻልም (እስካሁን ባለኝ መረጃ) ፡፡


ይህ ሲያጋጥም በውጭ የሚኖር ቤተ ዘመድ ወይም ማንኛውም ሰው ክፍያውን እንዲፈጽም ማድረግ ይቻላል ፡፡ ከዚህ በቀር ክፍያ ነክ ጉዳዮች ጋር መነካካት ገንዘብ ለመበላትም ሊያጋልጥ ስለሚችል ጥንቃቄ ያስልፈልጋል ::

5. የትምህርት አይነት እና ቦታ መምረጥ

መማር የፈለጋችሁት የትምህርት ደረጃ ድግሪ ፣ ማስተርስ ወይስ ፒኤችዲ ነው ?። መማር ያሰባችሁት ምን አይነት ትምህርት ነው ? ወደ የትኛው ሀገር ሄዳችሁ መማር ነው የፈለጋችሁት ? እነዚህን ወሳኝ ጥያቄዎች ከመለሳችሁ የነፃ ትምህርት አሰሳችሁን ጊዜ በጣም በተሻለ ሁኔታ ትጠቀሙበታላችሁ።


6. ነጻ የትምህርት እድል ለሰቃይ እና ለሐብታም ተማሪ ብቻ ?


ሰቃይ ተማሪ መሆን ባብኛው የነፃ ትምህርት እድል ለመሞከር ማነሻሻ ሲሆን ይታያል ባብዛኛው ጥሩ ውጤት ያለው ተወዳዳሪ የሆኑት እድሎች አግኝቶ የማለፍ እድልም ይኖረዋል።


ነገር ግን የነፃ የትምህርት እድል መለኪያ መስፈርቱ ውጤት ብቻ ባለመሆኑ አጥብቆ የፈለገ ማንኛውም ተማሪ ሊያገኝ ይችላል። መዘንጋት የሌለበት ግን አንዳንድ የትምህርት እድሎች ለከፍተኛ ውጤት ተማሪዎች የሚዘጋጁ በመሆናቸው ለይቶ እና ራስን አውቆ ማመልከቱ ጌዜን ይቆጥባል ባይ ነኝ።

7. እውን ነጻ የትምህርት እድል የነጻ እንጀራ?


አስቡት በሚሊየን የሚገመት ገንዘብ የሚፈጅ እድል ነው የምታገኙት ታድያ ይሄ እድል ዝም ተብሎ የሚታፈስ አይደለም። እድሉን ለማግኘት በአለም ላይ ካሉ በርካታ ተማሪዎች ጋር መወዳደርም ስለሆነ በትጋት በተደጋጋሚ መሞከር ሊኖርብን ይችላል።


Betelhem Abay studied at University of Maine

ዶክመንቶችን ማዘጃት ፣ አስፈላጊ የሆኑ ፈተናዎችን መፈተን ፣ ልምድ ካላቸው ልምዳቸውን መጋራት ወዘተ. እድሉን ለማግኘት መክፈል ያለብን ዋጋ ሆኖ እናገኘዋለን። “no free lunch” ይሉት ነገር ነው።


ስናጠቃልለው ከላይ የጠቀስኳቸውን ነጥቦች ግምት ውስጥ በማስገባት እድላችሁን ብትሞክሩ ለራሳችሁም ለሀገራችሁም ይበልጥ ጠቃሚ ሰው ትሆናላችሁ። መልካም ሁሉ ከናንተ ጋር ይሁን።


ለሚጠቅማቸው ማጋራት አትርሱ ሼር ሼር ይደረግ መልካም እድል። አመሰግናለሁ።


ሐሳብ ዋጋ አለው !

Idea Matter !


#ashruka #ashrukaacademy